top of page

Messages

ለውድ ወንድሜ አቶ ፍሬው፣
አስቀድሜ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓም በወጣት ናትና ብሩክ (Natna Brook) ኃይሉ በተደረገው የቀብር ሥነ ሥርዓት ባደረከው የማስተባበርና መምራት ተግባር በበኩሌ ላቅ ያለ ምሥጋና ሳቀርብልህ በአክብሮት ነው
በይበልጥ በኖርዝ ካሮላይና ግሪንስ ቦሮ ከተማ ማህበረሰብ ሳይለያዩ በአንድነት ኢትዮጵያውን ኤርትራውያን ያሳዩት ትብብር እጅግ የሚያስቀና ነው
ይህ ብቻ ሳይሆን በቤተ ሃይማኖት አባት እና ሌሎች አገልጋዮች ቤተሰቡን ለማፅናናት በመከባበር ያደረጉት መስተጋብር የሚያስመሰግናቸው ነው::
ይህ ሁሉ ሲደረግ የመርሃ ግብሩ ሰዓት ሳይዛነፍ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሞ በማህበረ ሰቡ አዳራሽ ጠበል ጠዲቅ መስተንግዶ የሁሉም ማህበረሰብ አባላት(ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን) መስተግዶ እጅግ የሚያስመሰግን ሆኖ አግኝቻለሁ::
በመጨረሻም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መስካሪ እንደሆናችሁ ሥራችሁ መስክሯል ብዬ ተረድቻለሁ:: ላደርጋችሁት ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ብድራችሁን በአለም ይክፈላችሁ::
ብርሃነሥላሴ

image.webp

© 2035 by Natural Remedies. Powered and secured by Wix

  • b-facebook
  • Twitter Round
bottom of page